About us/ስለ እኛ

Naphtalim.com

እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ሰለወደደንና ከሀጥአትና ከዘላለም ሞት ሰለዋጀን በፍቱ ቆመን እናገልግል ዘንድ እድል በማግኘታችን በጣም ደስይለናል፡፡ ከእኛ የሆነ ምንም ነገር ባይኖርም ከእርሱ በሆነው ለእርሱ እናገለግለው ዘንድ ባለፉት 30 አመታት እርሱ ለእኛ የከፈለውን ዋጋ ያህል ባይመጥንም ብዙ ውጣውረድ ሸለቆና ተራራ ለመውጣት ችለናል፡፡ በሕይወታችን ያየነውን የእርሱን ችርትና ምህረት በእነዚህ አመታቶች የማይረሱን ሆኖ እስከ ዛሬ ጉልበት ሆነውናል፡፡ አንድን ሰው ከዘላለም ሞት እንመልሰው ዘንድ የእርሱን የመስቀል ሞት ፍረው በእኛ ይታይ ዘንድ ችላ እንዳንል ነፍሳችን ጥራለች፡፡ በምንም በማንም መጠን ሳይሆነ ጌታ ለእኛ በሰጠን መጠን ማገልገልን በመረዳት አሁንም የቀረንን ዘመን እንደምናገለግለው እምነታችን ሙሉ ነው። የእግዚአብሔር ፀጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፡፡ 7 እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ አንድ የጸጋ ስጦታ እንኳ አይጎድልባችሁም፤ 8 እርሱም ደግሞ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል። 9 ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው። 1ኛቆሮ 1፡7 - 9


የንፍታለም የዘማና መንፈሳዊ ቅነ ዲህረ ገጽ አላማና ራእይው

ንፍታለም የመንፈሳዊ ዘማና የቅነ ዲህረ ገጽ ታሰበው የተዘጋጀው መንፍሳዊ መዝሙሮችን ፤ መንፍሳዊ ሰብከቶችንና መንፍሳዊ ትምህርቶችን ለተጠቃም ለመልቀቅ ነው፡፡ ለዚህ ሥራ ያነሳሳኝ ለረዥም ጊዜ የቢሮ ሥራ ስሠራ በነበርኩበት ወቅት መዝሙሮችን ኦንላይን በምፈልገው ምልኩ ለመስማት እቸገር ነበረ፡፡ ጃንክ ማስታወቅያ ያልበዛበት መንፈሳዊ የአውዲዮ ገጾች እፈልግ ነበረ በወቅቱ ዩቱብና ለሎችም ጥቅቶች ብኖሩም ግን እኔ በሚፈልገው መልኩ ለማግኘት ያስቸግረኝ ነበረ፡ በተቃራንው ዓለማዊ የዘፈንና ፍልም እጅግ ጣም ብዙ ነበሩ፡፡
ከዚህ በመነሳት ማስብ ጀመርኩኝ፡ ዓለማችን ለምን በምንፈሳዊ መሣራ አንሞልም ብየ አሰብኩ፡፡ ባለችኝ ትንሸ የዊብሳይት ዲዛይን እውቀት ተጠቅመ መንፈሳዊ ገጾች መሥራት ጀመርኩ ያነ ሁነታው ምቹ ሰላል ነበሩ ዊብሳይቱን መልቀቅ አልቻልኩም አሁን ሁነታዎች ምቸሁ ሰሆኑልን ለሁሉም መጠቀም በሚችሉት መልኩ ለቅቃልሁ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን፡፡ አንድአንዱ ከስኦል ደጅ ለማድረሰ ከተጋ እኛ ወደ ህይወት ደጅ ለማድረስ ዳታኛ መሆን አይገባንም እያልኩ ቀጥለው ያለውን ጠቅስ ያንብቡ እላለሁ፡፡ 11 ልጆቼ ሆይ፥ በፊቱ ትቆሙና ታገለግሉት ዘንድ፥ አገልጋዮቹም ትሆኑ ዘንድ፥ ታጥኑለትም ዘንድ እግዚአብሔር መርጦአችኋልና ቸል አትበሉ። (2ዜና 29 :11) 11 My sons, be not now negligent: for the Lord hath chosen you to stand before him, to serve him, and that ye should minister unto him, and burn incense.(2Chr 29 : 11 )

ራዕይው

ዛሬ በአለማዊ ሚድያ ገበያ ላይ ተለቀው ለመንፈሳዊ ክብር በማይመጥን ሁነታ እየተሸጠው ያለውን መንፈሳዊ መዝሙሮችን ወደ መንፈሳዊ ቤት በማምጣት ሙሉ አገልግሎት አግኝተው ክርስቶስ በሚሸት ቤት ውስጥ ለሽያጭ ማቅረብ አለብን ብዬ አምናለሁ፡፡ እግዚአብሔር ብረዳን ወደፍት በዚህ ሁነታ ላይ እንሰራበታልን፡፡ ዛሬ መዝሙር እንድሸጥላቸው ዘማሪዎቻችን የሚጠቀሙባቸው ድህረ ገጾች ብዙዎቻቸው የክርስቶስ ተቃዋም ደጋፍ ናቸው። መዝሙር ለእነርሱ የሚሸጥ ሸቀጥ መሆኑን እንጅ የእነዚህ መዝሙሮች መንፈሳዊ ክብርና ዋጋ የሚረዱትና የምቀበሉ አይደሉም። ስለዚህ የተሻለ መንፈሳዊ በት ብዘጋጅ የተሻለ ይሆናል ብለን እናምናለን፡፡ይህንንም ለማሳካት ተግተን እንሠራለን

ማሰሰቢያ፦

በኒፍታለም ድህረ ገጽ ላይ ያሉት መዝሙሮችን በተመለከተ እነዚህ መዝሙሮች ለረዠም አመት በገንዘብ ግዠ ተሰብስበው በእኛ ዘንድ የምገኙ ከሰቶችና ሲዲዎች ቅጅ ናቸው፡ እነዚህ መዝሙሮች በዚህ ገጽ ላይ ለሽያጭ የምቀርቡ አይደሉም፡ ወይም ዳውን ሎድ አናስደርግም ግን ዳውንሎዲ ማድረግ ብትፈልጉ የዘማርዎችን የሽያጭ ገጾች ፈልጋችሁ ትጠቀሙ ዘንድ እናሳስባለን
በመዝሙሩ ከተባረካችሁ ዩቱቦቻቸውን ሄዳችው ላይክና ሸር አርጉላችው እነዚህ እግዚአብሔር የተጠቀመባቸው አገልጋዮች እንድረዱ እንድባረኩ የዘወትር ምኞታችንና ፀሎታችን ነው።